the green flood

the green flood

Sunday, May 18, 2008

የአበበ፡ቢቂላ፡አትሌቲከሰ፡ክለብ፡በአንትወርፕን፡አሸነፈ፡

አፕሪል፡20/2008 በቤልጂየም፡አገር፡ሁለተኛው፡ከተማ፡በሆነችው፡በአንትወርፕን፡በተዘጋጀው፡የማራቶን፡ዱላቅብብል፡በዚያው፡ከተማ፡የተቋቋመው፡የአበበ፡ቢቂላ፡ክለብ፡በወንዶች፡ቀድሞ፡በመግባት፡ድልን፡ተቀዳጅቷል።ክለቡን፡በመወከል፡የተወዳደሩት፡አትሌቶች፡ከቤልጂምና፡ከኔዘርላንድ፡ተውጣጡ፡ናቸው።

ሀይሌን፡እንቅደመው፡

የፊታችን፡ሳምንት፡በጃፓን፡አገር፡በሚዘጋጀው፡የህይሌን፡እንቅደመው፡የማራቶን፡ዱላ፡ቅብብል፡ጃፓናዊያን፡በመሳተፍ፡የሚያሰባስቡት፡ብር፡ለአፍሪካ፡መርጃ፡እንደሚውል፡ተረጋግጦዋል፡አትሌት፡ ሀይሌ፡ገብረስላሴ፡በዚያን፡ወቅት፡ለኦሎምፒክ፡ሰአት፡ለማምጣት፡በሆላንድ፡አገር፡ሄንጌሎ፡10000ሜትር፡ስለሚወዳደር፡በእለቱ፡የራሱን፡ማራቶን፡ውድድር፡በቪድዬ፡መልክ፡እንደሚልክላቸው፡ተናግሮአል፡ተወዳዳሪዎች፡በዳኛ፡ሚወሰንላቸውን፡ርቀት፡ለሶስት፡በመሮጥ፡የሀይሌን፡ክብረወሰን፡ለመስበር፡ይሞክራሉ፡ተብሎ፡ይጠበቃል።