the green flood

the green flood

Friday, July 10, 2009

አትሌት ዲሶ ዴሲሳ እና አትሌት ቱርቦ ቱሞ አረፉ

አትሌት ዲሶ ዴሲሳ በሚኖሩበት ሃገር በስዊዘርላንድ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አትሌት ቱረቦ ቱሞ ደግሞ ከአዲስ አበባ ተነሰቶ ወደ አዋሳ ሲገሰግስ የነበረ አውቶቡሰ ተገልብጦ በውስጡ ከነበሩት 59 ሰዎች ውስጥ እሳቸው እና ሌሎች 18 ሰዎች ሞተዋል
አትሌት ዲሶ ዴሲሳ የቀብር ስነስርአት እዚያው በሚኖሩበት ሀገር በስዊዘርላንድ በሎዛን ከተማ በርካታ ኢትዮጲያዊያን እና የውጭ ሀገር ወዳጆቻቸው በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ያትሌት ቱርቦ ቱሞ የቀብር ስነስርአት በአብዛኛው በሚቀመጡበት በአዋሳ ከተማ ተፈጽሞአል
ሁለቱም አትሌቶች ከብርቱ አትሌትነታቸው ሌላ በጋራ የሚታወቁበት በቀልድ አብዝቶ አዋቂነታቸው እና በተግባቢነታቸው ነበር አትሌት ዲሶ በሚኖሩበት ሀገር በወገን ደጋፊነታቸው እና ሰብሳቢነታቸው እጂግ የተመሰገኑ ደግ ሰው ነበሩ ለዚህም በአውሮፓ ከሚኖሩ ኮሚኒቲዎች በታዋቂ አትሌቶች ተወካይነት አበባ አኑረውላቸዋል
ETHIOPIAN ATHLETES /
ልባዊ ሃዘኑን ይገልጻል