the green flood

the green flood

Saturday, July 1, 2017

ብርሃኑ ግርማ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ባለ ውለታ ነው

በጃን ሜዳ ላይ በብርሃኑ ግርማ አማካኝነት ተሰባስበው በአንድ ላይ ይለማመዱ ከነበሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ክለብ አትሌቶች መካከል ከግራ በኩል ግርማ ኡርጌ ፣ ታደሰ ከበደ ፣ወልደ አረጋይ ሁንዴ ፣ገረመው ፣ከሚል ፣ታደሰ አበበ ቢቂላ ፣መስፍን ዮሐንስ፣ መስፍን ጣሰው ፣አለማየሁ፣ተስፋዬ ዘለቀ፣ እና ፍቃዱ ይፍሩ ይገኙበታል
 በዚያን  ወቅት ብርሃኑ ግርማ በራሱ ፍላጎት ያለምንም  የደመወዝ ክፍያ ብዙ ወንዶች እና ሴት አትሌቶችን  ከመላው አዲስ አበባ ሰፈሮች ፣ ክለቦች  እና ትምህርት ቤቶች አንድ ላይ በማሰባሰብ በጃን ሜዳ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  ሜዳዎች ላይ  በተለያዩ  ርቀቶች ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ የብቃት ስልጠና ይሰጥ ነበር   የቀድሞው የኢትዮጵያ ባህር ኁይል  ኦፊሰር የሆነው ብርሃኑ ግርማ   
በአስር ሺህ እና በአምስት ሺህ  ሜትሮች እንዲሁም በሃገር አቋራጭ  ውድድሮች  በብዙ ኢተርናሽናል መድረኮች  የበርካታ ድሎች ባለቤት  የሆነ  ጀግና አትሌት ነው  ከነዚህም ውስጥ የሞስኮ ስፓርታኪያድ  እና ተከታታይ  ስድስት ዓመታት የአንጎላ ድሎቹ  ከብዙ አድናቂዎቹ አእምሮ  የማይጠፉ  ሲሆን  በዘመኑ  አረንጓዴው ጎርፍ( The green flood)የደጋው በራሪዎች ፣ የሰማይ ዳርቻ የማይበግራቸው  የሚል መጠሪያ የተሰጠው የጀግኖች አትሌቶች  ቡድን አካል ነበር 
ብርሃኑ ግርማ የኢትዮጵያን  አትሌቲክስ ስፖርት ለማሳደግ ክፍተኛ ድርሻ ካበረከቱት የስፓርቱ ባለውለታዎች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ያልተነገረለት  ጀግና ነው   በተለይም ለሴት አትሌቶች በብዛት ወደ ውድድር መድረክ መምጣት  ሰፊ መንገድ የከፈተ  ድንቅ አትሌት እና አሰልጣኝ  ነው  በአዲስ አበባ ክለቦች  ሻምፒዮና  እና በኢትዮጵያ ሻምፒዮናዎች  የሴት አትሌቶች  ቁጥር በአጭር ግዜ ጨምሮ ከወንዶች  እኩል  እንዲሆን  በግሉ ከፌዴሬሽኑ በላይ የሰራ ግን ምስጋና የተነፈገ  እንዲሁም  ስፖርቱን የበለጠ ተወዳጅ እና ተዘውታሪ  ለማድረግ በነበረው እቅድ በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች ውድድሮችን በማዘጋጀት የህዝቡን ተሳትፎ ለማጎልበት  በማሰብ ያቀረበው ጥያቄ  እኛም ከጎንህ አለን በርታ በማለት ፈንታ  ይህ የኛ ያልሆነ የባእዳን  ባህል  ነው  ውድድር  ከፌዴሬሽን ውጭ ማንም ማዘጋጀት አይችልም  በሚል ምላሽ እውቅናን  በመንፈግ ተስፋ አቆራጭ ምላሽ  የተሰጠው  የዛሬውን  የነ  ኍይሌን  ውድድር  ዓይነት  ገና ድሮ ያሰበ  እና  እድሉን ባይነፈግ  ኖሮ  ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ሰው ይሆን ነበር 
  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን  ለዘመናት ያዳበረው ክፉ ባህል ሆነና እንደነዚህ ያሉትን ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ  ታታሪ ሰዎችን  በማቅረብ ፈንታ ማራቅ  ስፖርቱን የሚጠቅሙትን  ሳይሆን በስፖርቱ የሚጠቀሙትን እና  የስርአቱ ደጋፊ የሆኑትን  ብቃት የሌላቸው ሰዎችን  በዙሪያው የሚሰበስብ  ቤት ስለሆነ  እንደነዚህ  ያሉ  ጠንካራ  ኢትዮጵያውያን  እድሉን ተነፍገው  የአትሌቲክስ  ስፖርታችን   እድገት  አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደ ኋላ እያለ   እንዲኖር  ተደርጓል