the green flood

the green flood

Wednesday, August 14, 2013

በ1956 ዓ ም እኤአ የሜልቦርን ኦሊምፒክ በማራቶን ኢትዮጲያን ወክሎ የተወዳደረው በሻዬ ፈለቀ

ከሜክሲኮ  አደባባይ  ወደ ልደታ ሲኬድ ከተግባረ ዕድ  ወረድ ብሎ  ሞኤንኮ    በጥበቃ  ስራ ላይ  የነበሩት   አንጋፋ  አትሌት ለዚህ ሁሉ ድል እና ጀግንነት ፈር ቀዳጅ  እንደነበሩ  ሳስብ  እንደ ባለወርቅ  ሜዳሊያዎቹ  ጀግኖች ልቤ ያከብራቸዋል።
  ተግባረዕድ ስማር  ማታማታ እየሄድኩ አያቸው ነበር  ብዙ ታሪክ ይነግሩኝ ነበር ፡ የተረሱ  ጀግና  ናቸው ፡ ትዝ ከሚሉኝ ውስጥ ፡ አንድ ቀን  እንዲህ  አሉኝ  ፡ይሄውልህ  ልጄ ለመኖር መስራት  አለብህ  አለበለዚያ  ደግሞ ጥሩ  ውርስ  ሊኖርህ  ይገባል   ፡ይሄው  ለመኖር  ስል  ውርጭ  እየገረፈኝ  አድራለሁ ፡፡
 አትሌቲክስ  ፌዴሬሽንን  በተደጋጋሚ  ድጎማ እንዲያደጉልኝ  ጠይቄ  ተከለከልኩ  በመጨረሻ  ዘበኝነት  እንኳን  አስቀጥሩኝ   እና እዚሁ ካምቦሎጆ  ብርድ እና ጠሃዩ ይለብልበኝ  ቢያንስ  ቢያንስ  የምወደውን  ስፖርት  ሲለማመዱ አያለሁ ብዬ ለመንኩ ፡  ኧረ ተወው ልጄ ብለው ድንገት ትክዝ ብለው ቀሩ ፡ ባሻዬ  ምነው  ስላቸው ፡ ባዘነ ፊት ቀና ብለው   እነ እከሌ  አልልህም   ይሸሹኝ  ጀመር  ብቻ አንድ ሰው አለ  ነፍሱን ይማረውና  ያ  ይድነቃቸው  ተሰማ  የትም  ይየኝ  አክብሮ  ሰላም ብሎኝ ፡  ትቶኝ ይሄድ መሰለህ ፡ እቤቱ  ወስዶኝ   በእጄ ብሎኝ  ከቁምሳጥኑ መዞ ሙሉ ልብስ  ከጫማ ጋር  ሸልሞኝ  ይሸኘኛል   ብለው  አሁንም  ትክዝ  አሉ ፡፡
  በአጋጣሚ  አስተማሪ የሌለ  ቀን  ወይም በእረፍት ሰዓት ሁሌ ወደ እሳቸው  ጋር እሮጣለሁ  እኔም እሮጥ ስለነበረ  በስፖርቱ ዙሪያ  የሚነግሩኝ  ነገር እና ምክራቸው ይስበኛል ፡በዚያ ወቅት  እኔ በትንሽ  የኪስ ገንዘብ  የምሮጥ  እና ከዚያችው  ከፍዬ  የምማር  ስለነበር ልረዳቸው  ባለመቻሌ  አዝን ነበር ፡፡
  ስፖርተኛ እና አዳኝ  አንድ ነው በለስ የቀናው  እለት ይዞ ይገበል  ጉሮወሸባ  ይባልለታ    ያልቀናው ቀን ደግሞ  ዝም  ነው  ፡ ስለዚህ  ስትሸነፍ ብዙ አትዘን  ሌላ ቀን አለና ፡፡እንዲ አይነቱ ለዛ ያለው ምክራቸው ነበር  የሚስበኝ፡ ይህ ከሆነ 22 ዓመታት አልፎልታል


               ነባር አትሌቶች እና እንደ ስንታየሁ እና ገብሬ   ያሉ እንዲሁም አትሌቶች  በድል ሲመለሱ  ከዱሮ ጀምሮ  በከፍተኛ  ወጭ አቀባበል  ሲያደርጉና  በብዙ ነገር  ጀግኖችን  ሲያስታውሱ  የኖሩትን እንደ አቶ አብይሴሎም  ያሉ  የሃገራችን አትሌቲክስ ባለውለታ የሆኑትን   በአንዳንድ  ዓለም አቀፍ የውድድ መድረኮች ላይ  ለንግድ ከሚጓዙ ኮሚቴዎች  ቁጥር ቀነስ በማድረግ በክብር ተጋባዥነት  አልፎ አልፎ ቢሄዱ ውለታቸው በመጠኑ ተከፈለ ማለት ነው  እና   ይታሰብበት አደራ ፡፡



Saturday, August 3, 2013

የሞስኮ ኦሊምፒክ ድል በእጥፍ ድርብ ድሎች ዛሬም በሞስኮ ይደገማል

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን  እንዲሆን እየተመኘን    በሞስኮ  ኦሊምፒክ  በይፍጠር የተገኘው ድርብ ድል   በቱራ    በከዲር  በቆቱ   የመጣው   መዳልያ  በብዙ እጥፍ በርክቶ   በዮሃንስ መሀመድ   በከበደ ባልቻ  በሁንዴ  ጦሬ    በሃሰን   የታየው  ፍልሚያ
ጎልብቶ   ለበለጠ  ድል እንዲያበቁን  በሞስኮ የምትኖሩ  ኢትዮጵያዊያን  የተለመደው  ድጋፋችሁ  እንዳይለያቸው   አደራ እንላለን


Saturday, May 11, 2013

የአትሌት ተወካዮች አትሌቱን መች ወክለው ያውቃሉ

         በተለያዩ ግዜያት  ችግራችሁን  ለመንግስት ለማሰማት ከፈለጋችሁ  የአትሌቶች  ተወካይ   ሊኖራችሁ  ይገባል
ተብለን  ከመካከላችን  ወከልን   ግን  እዚያ  ሲደርሱ የአትሌቶች  ተወካይ  መሆነቸው  ቀርቶ   በአትሌቱ   ላይ የመንግስት
ወኪል  ይሆኑና  ችግራችንን  ማድረሳቸው  ቀርቶ  እንዲያውም  እንድንፈራቸውና  ከመናገር  እንድንቆጠብ  ሆነናል
     ይህ  በተደጋጋሚ የታየ  ነገር ነው   ከኛ ጋር  ያላቸው  ግንኙነት  ከበላይ  መልእክት  ወይም አዲስ  ትእዛዝ ሲመጣ
ለመንገር ብቻ  ነው  ከተመረጡ  ቦኁላ አነጋገራቸውና  የሚጠቀሙአቸው  ቃላቶች  እንኳን  ሳይቀር   ከቀድሞው  የተለየ   እየሆነብን   ተቸገርን    ማን እነሱ   ፊት ይናገራል    ያስፈራል እኮ  እኛው መርጠን በእኛው ላይ  .....................

 ህዝቡ  ሁሉ አትሌቱ   የደላው  ምንም  ችግር  የሌለው  አድርጎ   ነው የሚያየው   ኧረ  ስንት ሰሚ  ያጡ  አሰልጣኞች እና
አትሌቶች   አሉ  አሁንማ  የቻለ  ይኮበልላል   ያልቻለው  ደግሞ   እውነተኛ  ተጠሪውን  እስኪመርጥ   እና  ሰሚ እስኪያ
ገኝ ድረስ  ዝምታን  መርጦአል  
  ቀን እስኪወጣልን   ድረስ  ሁኑ   ያሉንን  መሆን  ነው  ያለዚያማ  ይህቺ ገባ ወጣ  እያሉ  መቀራረምም  ትቀራለቻ   ሩጡ
ሲሉን  መሮጥ   ቁሙም  ከተባለ  መቆም    ስብሰባ  ላይም  ፊቱ   ፈታ ያላለ  ሰንበትበት  ብሎ  ነገር   ይመጣበታል  ያን
ፍራቻ  መሣቅ  ነው  ምን  እናድርግ    እንዲያውም    ሁሌ ለቅሶ  ቢኖር  እኮ እህህህህህ    ብለን   በሰበቡ   ይወጣል  ነበር




 

Sunday, March 17, 2013

የመስቀል ዓደባባይ አትሌቶች

           በኖቬምበር  ወር 2012 ላይ በመስቀል አደባባይ በኩል  ሳልፍ  በርከት ያሉ  አትሌቶች ደረጃውን  ወደ ላይ ወደ ታች  እየተመላለሱ  ሲለማመዱ  አይቼ  ቀልቤን ስለሳበኝ   ቀረብ  አልኩና  ሰላምታ ከተለዋወጥኩ  በኋላ  ለምታለማምዳቸው   ሴት  አንዳንድ  ጥያቄዎች አቀረብኩ   ለምሳሌ  ያህል    የት ክለብ ናችሁ ?..........
 የማረሚያ  ፖሊስ  አትሌቶች እንደ ሆኑ እና   መስቀል ዓደባባይ  አቅራቢያ ብሆራዊ  ሆቴል  ጂም ናዚየም ለመግባት እያሟሟቁ  እንደሆነ ተረዳሁ  ብዙ  የማውቃቸውን  ሰዎች ስላላየሁ  አሁንም  ጥያቄ አቀረብኩ ፣ የረጅም ርቀት ቡድን  ዛሬ እዚህ ስለማይሰሩ እነሱ የሉም አለችኝ   እመሰግናለሁ  ብዬ   መንገድ    ከጀመርኩ  በኋላ  የህብረት  ጂምናስቲክ  አሰራራቸው   ስለሳበኝ   እና  እትዝታ ስለቀሰቀሰብኝ  አንድ ፎቶ  ለምን አላነሳም ብዬ   ካሜራዬን  ሳስተካክል ከመካከላቸው አንዱ ያዙኝ ልቀቁኝ ኣለ  ምን ሆኖ ነው  ምን  ተከሰተ ብዬ  ማንሳቱን  ኣቋረጥኩ ፣

    በዚህ ግዜ ሌላው  ቀረብ ብሎ  እዚህ አሁን ዲሞክራሲ  ስለሆነ    መናገር እና መከልከል መብቱ ነው  ኣለኝ   ተመስጌን
  ዲሞክራሲን  በዓይኔ አየሁ ብዬ  የነሳሁት ሁለት  ፎቶዎች  እያሳየሁ   ከካሜራዬ ላይ አጥፎቼ   ሄድኩ፣
   በየስታድዮሙ  ካሜራ ኣንግቦ  እየገባ ፎቶ  የሚያነሳው ተመልካች እና  የፕሬስ  ሰው  ሁሉ አትሌቱን  እያስፈቀደ  ኖሮኣል  እንዴ?  እኔን  ግን  ብዙ ሰዎች ብዙ  ጊዜ  ፎቶ  ሲያነሱኝ  እያስፈቀዱኝ ኣልነበረም፣  እናንተስ ???????
ባለካሜራዉ  ምናልባት   ፈረንጅ  ቢሆን ኖሮ  ደጋግመህ አንሳን ብለው እንደሚለምኑት   እገምታለሁ ፣
     





  

Friday, February 8, 2013

Ibrahim hussen

Tuesday, February 5, 2013

HELP DR WOLDEMESKEL KOSTRE

https://www.youtube.com/watch?v=Sq08ZiKoiUw