the green flood

the green flood

Friday, August 29, 2008

አትሌቶቻችን፡ለዓለም፡ግማሽ፡ማራቶን፡ውድድር፡ ይዘጋጃሉ።

መስከረም፡21ቀን፡የዛሬ፡ሳምንት፡በቤልጂየም፡ዋና፡ከተማ፡በብራስልስ፡ለሚካሄደው፡ዓመታዊ፡የዓለም፡ግማሸ፡ማራቶን፡ውድድር፡አትሌቶቻችን፡በከፍተኛ፡ዝግጅት፡ላይ፡መሆናቸው፡ተገለጠ።
ውድድሩ፡የሚካሄደው፡በሁለቱም፡ጾታ፡ሲሆን፡በወንዶች፡የአዋቂና፡የወጣት፡ተወዳዳሪዎች፡ተካፋይ፡ይሆናሉ፡፡
በዚህ፡ውድድር፡በሴቶች፡ሶስት፡-በአዋቂ፡ወንዶች፡አምስት፡በወጣት፡ወንዶች፡አራት፡በድምሩ፡12አትሌቶች፡ዝግጅታቸውን፡እያጧጧፉ፡ናቸው፡፡
በአዋቂ፡ወንዶች፡ለዚህ፡ውድድር፡የተመረጡት፡ኪዳኔ፡ገ/ሚካኤል፡ አዱኛ፡አጥናፉ፡ ወልደስላሴ፡ሚልኬሳ፡ ፍራንሷ፡ወልደማርያምና፡ ይኩን፡ገ/መስቀል፡ናቸው፡፡

በወጣት፡ወንዶች፡የተመረጡት፡ ብሩክ፡በቀለ፡ ተገኑ፡አበበ፡ ፍቃዱ፡ይፍሩና፡፡ልኡልስግድ፡ወልደማሪያም፡ሲሆኑ፡በሴቶች፡
የሚካፈሉት፡ፋንታዬ፡ሲራክ፡፡ አይሻ፡ጊጊና፡ አሰለፈች፡አሰፋ፡መሆናቸው፡ታውቋል፡፡
የዓለም፡ግማሽ፡ማራቶን፡ውድድር፡በተለያዩ፡ሃገሮች፡በያመቱ፡የሚካሄድ፡ሲሆን፡አትሌቶቻችን፡በተካፈሉብት፡ቦታ፡ሁሉአጥጋቢ፡ውጤት፡እያስመዘገቡ፡መመለሳቸው፡ይታወሳል፡፡ በዚህ፡ውድድርም፡ተመሳሳይ፡ድል፡እንዲያስመዘግቡ፡ዝግጅት፡ክፍላችን፡
መልካም፡ምኞቱን፡ይገልጣል፡፡
አዲስ፡ዘመን፡ መስከረም፡ 14 ቀን 1986 ዓመተ፡ምህረት፡