the green flood
Thursday, January 13, 2011
በአዲስ አበባ የአትሌቶች ስብሰባ ተደረገ
ነባር እና ልምድ ያላቸው አትሌቶች ለአዲስ እና ለወጣት አትሌቶች ልምዳቸውን ያካፈሉበት ይህ ስብሰባ የተዘጋጀውና የተመራው የአትሌቶች ተወካይ በሆኑት በገብረ/እ/ገብረ ማርያም እና በመሰረት ደፋር ነበር፣
በርካታ ታዋቂ እና የረጅም ዓመታት ልምድ ያላቸው አትሌቶች እና አሰልጣኞች ንግግር በማድረግ የወደፊቱ አትሌቶች
በስነምግባር የታነጹ እንሁም የሙያውና የሃገራቸው ፍቅር የሚታይባቸው እንዲሆኑ መክረዋል
ይህ የመማማር እና ልምድን የመካፈል ስብሰባ የሚቀጥል መሆኑን አትሌት ገብረ/እ/ገብረ/ማርያም እና አትሌት መስረት ደፋር አሰገንዝበዋል
ያብባል አበበ ቢቂላ በሚል ስም ከደርግ መውደቅ ቦኃላ ሁለት ሰላማዊ ሰልፎች እና ሁለት ከፍተኛ ስብሰባዎች በግዮን ሆተል ሳባ አዳራሸ
እና በብህራዊ ትያትር አዳራሾች ተደርጎ አትሌት ብሶታቸውን መግለጽ እንደቻሉ ይታወሳል
በእነ መቶ አለቃ ካሳ ባልቻ ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ሻምበል መሃመድ ክዲር ........ይመራ የነበረው የደርግ ዘመን የ አትሌት አመጽ ግን ለሁሉም ፈር ቀዳጅ ነበር