the green flood

the green flood

Wednesday, August 14, 2013

በ1956 ዓ ም እኤአ የሜልቦርን ኦሊምፒክ በማራቶን ኢትዮጲያን ወክሎ የተወዳደረው በሻዬ ፈለቀ

ከሜክሲኮ  አደባባይ  ወደ ልደታ ሲኬድ ከተግባረ ዕድ  ወረድ ብሎ  ሞኤንኮ    በጥበቃ  ስራ ላይ  የነበሩት   አንጋፋ  አትሌት ለዚህ ሁሉ ድል እና ጀግንነት ፈር ቀዳጅ  እንደነበሩ  ሳስብ  እንደ ባለወርቅ  ሜዳሊያዎቹ  ጀግኖች ልቤ ያከብራቸዋል።
  ተግባረዕድ ስማር  ማታማታ እየሄድኩ አያቸው ነበር  ብዙ ታሪክ ይነግሩኝ ነበር ፡ የተረሱ  ጀግና  ናቸው ፡ ትዝ ከሚሉኝ ውስጥ ፡ አንድ ቀን  እንዲህ  አሉኝ  ፡ይሄውልህ  ልጄ ለመኖር መስራት  አለብህ  አለበለዚያ  ደግሞ ጥሩ  ውርስ  ሊኖርህ  ይገባል   ፡ይሄው  ለመኖር  ስል  ውርጭ  እየገረፈኝ  አድራለሁ ፡፡
 አትሌቲክስ  ፌዴሬሽንን  በተደጋጋሚ  ድጎማ እንዲያደጉልኝ  ጠይቄ  ተከለከልኩ  በመጨረሻ  ዘበኝነት  እንኳን  አስቀጥሩኝ   እና እዚሁ ካምቦሎጆ  ብርድ እና ጠሃዩ ይለብልበኝ  ቢያንስ  ቢያንስ  የምወደውን  ስፖርት  ሲለማመዱ አያለሁ ብዬ ለመንኩ ፡  ኧረ ተወው ልጄ ብለው ድንገት ትክዝ ብለው ቀሩ ፡ ባሻዬ  ምነው  ስላቸው ፡ ባዘነ ፊት ቀና ብለው   እነ እከሌ  አልልህም   ይሸሹኝ  ጀመር  ብቻ አንድ ሰው አለ  ነፍሱን ይማረውና  ያ  ይድነቃቸው  ተሰማ  የትም  ይየኝ  አክብሮ  ሰላም ብሎኝ ፡  ትቶኝ ይሄድ መሰለህ ፡ እቤቱ  ወስዶኝ   በእጄ ብሎኝ  ከቁምሳጥኑ መዞ ሙሉ ልብስ  ከጫማ ጋር  ሸልሞኝ  ይሸኘኛል   ብለው  አሁንም  ትክዝ  አሉ ፡፡
  በአጋጣሚ  አስተማሪ የሌለ  ቀን  ወይም በእረፍት ሰዓት ሁሌ ወደ እሳቸው  ጋር እሮጣለሁ  እኔም እሮጥ ስለነበረ  በስፖርቱ ዙሪያ  የሚነግሩኝ  ነገር እና ምክራቸው ይስበኛል ፡በዚያ ወቅት  እኔ በትንሽ  የኪስ ገንዘብ  የምሮጥ  እና ከዚያችው  ከፍዬ  የምማር  ስለነበር ልረዳቸው  ባለመቻሌ  አዝን ነበር ፡፡
  ስፖርተኛ እና አዳኝ  አንድ ነው በለስ የቀናው  እለት ይዞ ይገበል  ጉሮወሸባ  ይባልለታ    ያልቀናው ቀን ደግሞ  ዝም  ነው  ፡ ስለዚህ  ስትሸነፍ ብዙ አትዘን  ሌላ ቀን አለና ፡፡እንዲ አይነቱ ለዛ ያለው ምክራቸው ነበር  የሚስበኝ፡ ይህ ከሆነ 22 ዓመታት አልፎልታል


               ነባር አትሌቶች እና እንደ ስንታየሁ እና ገብሬ   ያሉ እንዲሁም አትሌቶች  በድል ሲመለሱ  ከዱሮ ጀምሮ  በከፍተኛ  ወጭ አቀባበል  ሲያደርጉና  በብዙ ነገር  ጀግኖችን  ሲያስታውሱ  የኖሩትን እንደ አቶ አብይሴሎም  ያሉ  የሃገራችን አትሌቲክስ ባለውለታ የሆኑትን   በአንዳንድ  ዓለም አቀፍ የውድድ መድረኮች ላይ  ለንግድ ከሚጓዙ ኮሚቴዎች  ቁጥር ቀነስ በማድረግ በክብር ተጋባዥነት  አልፎ አልፎ ቢሄዱ ውለታቸው በመጠኑ ተከፈለ ማለት ነው  እና   ይታሰብበት አደራ ፡፡