the green flood

the green flood

Saturday, August 12, 2017

ድንቅ አትሌቶቻችን አዲስ እና ፊጣ

አዲስ አበበ እና ፊጣ ባይሳ በበርካታ ዓለም አቀፍ እና የአህጉር ሻምፒዮናዎች ላይ ሃገራችንን በመወከል ተሰልፈው ድሎች የተቀዳጁ እጅግ ጠንካራ አትሌቶች ናቸው አዲስ አበበ እና ፊጣ ባይሳ በባርሴሎና ኦሊምፒክ ሁለቱም በየተሰለፉበት በ5000 እና በ10000 ሜትር ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ ሲያስገኙ በሃቫናው iaaf world cup በሌጎስ እና በካይሮው የአፍሪካ ሻምፒዮናዎች እንዲሁም በካናዳው በዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ከዚያም በበርካታ የሃገር አቋራጭ እና የጎዳና ላይ ውድድሮች በተደጋጋሚ በማሸነፍ በወቅቱ ብዙ የተባለላቸው አትሌትች ናቸው ፊጣ በባርሴሎናው ኦሊምፒክ እንደሚያሸንፍ የዓለም የስፖርት ሚዲያዎች ከፍተኛ ግምት ከማግኘቱም በላይ በኮምፒዩተር ትንበያም ሳይቀር ድሉ የሱ እንደሚሆን ብዙዎች እርግጠኛ ሆነው ነበር ለውጤቱ አለመሳካት ከባርሴሎን መልስ በሰጠው ኢንተርቪው እንደተናገረው ( ምን እንደሆንኩ አላውቅም እግሬ ውሃ ሆነ ) ብሎ ነበር ለውጤቱ መበላሸ ምክንያቱ ግን በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበት ሁኔታ እና በአብዮታዊው መንግስት ሚዲያዎች ከልክ ያለፈ ከስፖርትነት አልፎ የኢትዮጵያን ስም ለማደስ እንደሚሮጥ መሸነፍ ጨርሶ የማይታሰብ እንደሆነ ይለፈፍ ስለነበረ ይህ ሁሉ ተደራርቦ የስነልቦና መረበሽ እንደፈጠረበ ግልጽ ነበር አዲስ አበበ በጣም ጠንካራ አትሌት ሲሆን በአስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር በኢንዶኔዥያ ጃካርታ በተደጋጋሚ ያሸነፈ ከመሆኑም በላይ የርቀቱን ወሰን በመስበር በወቅቱ ከፍተኛውን የገንዘብ ሽልማት ያገኘ ባለትልቅ ዝና አትሌታችን ነው አዲስ በራሱ ጥረት እና በአሰልጠኝ ዶከተር ይልማ በርታ አባታዊ ምክር ስልጠና ድጋፍ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፎ ለሃገሩ እና ለራሱ ክብርን የተቀዳጀ ጀግና ነው በዚህ አጋጣሚ ለመንግስት ለሚዲያዎች እና ለደጋፊዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከልክ ያለፈ ሃላፊነት በአትሌቶች ላይ መጫን በአትሌቶች ላይ መረበሽን እንደሚፈጥር እና አንዳንድ አትሌቶች ክልምምድ ቦኁላ በቂ እረፍት እንዳያደርጉ ይልቁንም በመኝታ እና በእረፍት ሰዓታቸው እንዲጨነቁ ብዙ እንዲያስቡ ስለሚያደርግ እና ይህ ደግሞ ጥሩ ላለመሮጣቸው ምክንያት ስለሚሆን አናስጨንቃቸው እላለሁ (የቻልከውን ያህል ሞክር ከዚያ በላይ አክርማ አይደለህ አትሰነጠቅ) ይል ነበር አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አትሌቱ ነጻ ሆኖ በራሱ የበለጠ እንዲተጋሚያደርግ የስልጡን አባባል ነው