the green flood

the green flood

Friday, April 4, 2008

የቤተሰብ፡ውርስ፡እየሆነ፡የመጣው፡የሃገራችን፡አትሌቲክስ፡ስፖርት፡

ከአለፉት፡ጥቂት፡ዓመታት፡ወዲህ፡በተደጋጋሚ፡የምንሰማው፡የሃገራችን፡አትሌቶች፡ሩጫን፡የቤተሰብ፡ስራ፡የማድረግ፡ሁኔታ፡ከግዜ፡ወደ፡ግዜ፡እየጨመረ፡መጥቶአል።
ደራርቱ፡ቱሉ፡ከባርሴሎና፡መልስ፡በሰጠችው፡ቃለ፡መጠይቅ፡ከእኔ፡የበለጠ፡የምትሮጥ፡እህቴ፡አለች፡ብላ፡ነበር፡ሙሉ፡ቱሉ፡ግን፡አልገፋችበትም።
በተደጋጋሚ፡የዓለም፡ወጣቶች፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡ሻምፒዬን፡የነበረው፡የፍስሃ፡አበበ፡ወንድም፡ታደለ፡አበበ፡በተለይ፡በሃገር፡ውስጥ፡ችሎታውን፡አስመስክሮ፡ነበር።
ከ1500ሜትር፡እስከ፡ማራቶን፡ድረስ፡በዓለም፡ደረጃ፡ታዋቂ፡የነበረው፡የወዳጆ፡ቡልቲ፡ወንድሞች፡ገለቱ፡ቡልቲ፡እና፡ኩምሳ፡ቡልቲ፡እምብዛም፡አልተሳካላቸውም።
የጀግናው፡የበቀለ፡ደበሌ፡ወንድሞች፡ዘውዴ፡እና፡አሰፋ፡ደበሌ፡ወደ፡ኢንተርናሸናል፡መድረክ፡ሳይወጡ፡ቀሩ።
የታላቁ፡አትሌት፡የህይሌ፡ገብረስላሴ፡ወንድም፡ተክዬ፡ገብረስላሴ፡እና፡እህቱ፡የሺ፡ገብረስላሴ፡በዓለም፡ሻምፒዮናዎች፡የማይናቅ፡ውጤት፡አስመዝግበዋል፡በላይ፡ገብረስላሴ፡ግን፡አልተሳካለትም።
በአሜሪካ፡ሃገር፡ታላቅ፡ስም፡ነበረው፡፡የሃይሉ፡ኤባ፡ወንድም፡ጥላሁን፡ኤባ፡ሃገራችንን፡እስከ፡መወከል፡ደርሶ፡ነበር፡ግሩም፡ኤባ፡ግን፡ብዙ፡አልገፋበትም።
ጠንካራዎቹ፡ሃብቴ፡ጂፋር፡እና፡ተስፋዬ፡ጂፋር፡የሃገራችንን፡ስም፡በብዙ፡ቦታዎች፡በተደገጋጋሚ፡አስጠርተዋል፡አሁንም፡በማስጠራት፡ላይ፡ናቸው።
አሰፋ፡መዝገቡ፡እና፡አየለ፡መዝገቡ፡በጉብዝናቸው፡ከሃገር፡አልፎ፡በዓለም፡አቀፍ፡ደረጃ፡ተመሰከረላቸው፡ጠንካራ፡አትሌቶች፡እንደነበሩ፡የቅርብ፡ግዜ፡ትዝታ፡ነው።መኮንን፡ቱሉ፡እና፡ብርሃኑ፡ቱሉም፡እንዲሁ። world and olimpic marathon champion gezahgen abera and his yungest brother daneil abera who run under 2h10 . እንዲህ፡እያለ፡ሲቆጠር፡ብዙ፡ልንል፡እንችላለን፡የቀነኒሳ፡በቀለ፡እና፡ታሪኩ፡በቀለ፡ጉዳይ፡ገና፡እያስደነቀ፡ያለ፡የዘመናችን፡የአትሌቲክስ፡ዜና፡ነው፡ገና፡ብዙ፡እናያለን።
በታላቅ፡እህት፡በበቀሉ፡ዲባባ፡የተጀመረው፡የእጅጋየሁ፡ዲባባ፡እና፡የጥሩነሸ፡ዲባባ፡ገና፡ተነግሮ፡ሳያበቃ፡ትንሿ፡ገንዘቤ፡ዲባባ፡የወጣቶች፡አሸናፊ፡በመሆን፡የወርቅ፡ሜዳሊያ፡አስገኝታለች።ገና፡ከአንድ፡ቤተሰብ፡ሁለት፡ሲገርመን፡ዛሬ፡ጭራሸ፡አራት፡ሆነዋል ፣ ሲሳይ በዛብህ ፣ አለማየሁ በዛብሀ ፣አለምገና በዛብሀ፣ መስታወት ቱፋ ፣ ትእግስት ቱፋ ፣ ይህ፣የሚያመለክተን፡ሃገራችን፡ሁኔታዎቸን፡ብታመቻች፡ብዙ፡ድንቅ፡አትሌቶችን፡ማፍራት፡እንደምንችል፡ነው።በቤተሰብ፡እየታየ፡ያለው፡ሁኔታ፡ደግሞ፡ማንም፡አዲስ፡አትሌት፡በቀደምቶች፡ወይም፡በታላላቆቻቸው፡ከተደገፉ፡ያለምንም፡መሰናክል፡ብቃት፡ያላቸው፡አትሌቶች፡እንደሚወጣቸው፡ነው።

No comments: