the green flood

the green flood

Sunday, March 23, 2008

የኢትዮጵያ፡አትሌቲክስና፡አትሌቶች፡ከየት፡ወዴት።

የአገራችን አትሌቶች የማይካፈሉበት ውድድር አይደምቅም እነሱ በደርሱበት ቦታ ሁሉ ባንዲራችን ክፍ ብላ ትውለበለባለች ይህቺ ሃገር በየዘመኑ ዓለምን የሚያስደንቅ ችሎታ ያላቸው አትሌቶች አጥታ አታውቅም፣፣
የሃገራችን አትሌቲክስ ስፖርት የተጀመረው በጦር ስራዊቱ አካባቢ እንደሆነ የሚጠቁሙ ብዙ ማረጋገጫዎች እናገኛልን
ከ1956 አውስትራሊያው ኦሊምፒክ ጫወታዎች ማግስት ጀምሮ ማራቶን የሚል ቃል በብዛት ይስማ ጀመር፣፣ ሁለተኛው የሃገራችን የ1960 የሮማ ኦሊምፒክ ግን ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም የመጀመሪያው ኦሊምፒክ ድል ሆነ ከዚያም መቀጠል በ1964 ቶኪዮ በራሱ ጀግናው በአበበ ቢቂላ ተደገመ የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ ማራቶን የማራቶን ጉዳይ ሲነሳ ኢትዮጵያ የማይነጣጠሉ ሆኑ ከአራት ዓመት ቦሃላም ማሞ ሶስተኛውን የኦሊምፒክ ወርቅ ለሃገራችን አመጣ ማሞ በዚያ ብቻ አላበቃም በዘመኑ ነሃስም አስገኝቶልናል ፣፣
በእነ በሻይ ፈለቀ ገብረ የተጀመረው እነ አበበን ፣ ማሞን ፣ ደምስን ፣ሽበሺን፣ ተገኝ በዛብህን አስከትሎ ለነምሩጽ ይፍጠር ዘመን ስንደርስ ከማራቶን ወደ አስር አና አምስት  ሺህ ሜትር  በመሸጋገር   ኢትዮጵ ያዊያን  አትሌቶች  በየተሰለፉበት   የውድድ ር  መ ድረክ  ሁሉ  ድልን መቀዳጀት  የተለመደ  ሆነ ::
   


 

No comments: