the green flood

the green flood

Wednesday, March 26, 2008

36ኛው፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ሩጫ፡፡በኤዲንበርግ፡ይደረጋል።

እ.ኤ.አ.ማርች፡30/2008ዓ.ም፡ በሚጀመረው፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡ከሚሰለፉት፡ሃገሮች፡ውስጥ፡ጠንካራው፡ የኢትዮጵያ፡ቡድን፡መሆኑን፡ብዙዎች፡ይገምታሉ፡በዚህ፡በ36ኛው፡ኤዲንበርጉ፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡የኬንያ፡ቡድን፡ቢሳተፍም፡በሃገሪቱ፡በተፈጠረው፡የፖለቲካ፡ውዝግብ፡የተነሳ፡በስነልቦና፡ዝግጅት፡ከቀድሞው፡ባነሰ፡ጥንካሬ፡እንደሚቀርብ፡ይገመታል፡በቅርቡ፡በተደረገው፡የቤት፡ውስጥ፡የዓለም፡ሻምፒዮና፡ይህው፡ታይቶ፡ነበር።

የኤርትራ፡ቡድን፡በጠንካራው፡አትሌት፡ዘረሰናይ፡ታደሰ፡ዘንድሮም፡የአምናውን፡ድል፡ላለማስነጠቅ፡እንደሚተጋ፡ይጠበቃል።በመቀጠል፡የሞሮኮ፡ቡድን፡በሰልጣኝ፡ኢብራሂም፡ቡላሚ፡አማካኝነት፡በአዲስ፡መልክ፡የተመረጡ፡በአብዛኛ፡ወጣት፡የሆኑ፡አትሌቶችን፡ይዞ፡ይሰለፋል።

በዚህ፡ዓመት፡ከኤርትራው፡ዘረሰናይ፡በስተቀር፡ለኢትዮጵያ፡ቡድን፡ሌላ፡የሚያሰጋ፡እንዳሌለ፡ብዙዎች ፡ይተነብያሉ።በቀነኒሳና፡በጥሩነሽ፡የሚመራው፡የኢትዮጵያ፡ቡድን፡ በድል፡እንደሚመለስ፡ይጠበቃል።

No comments: