the green flood

the green flood

Monday, March 24, 2008

የኢትዮጵያ፡አትሌቶች፡የኦሎምፒክ፡ተሳትፎ፡

ኢትዮጵያ፡አትሌቶችን፡ለኦሎምፒክ፡ውድድር፡መላክ፡የጀመርችው፡እንደ፡አውሮፓዊያን፡አቆጣጠር፤በ1956 ዓ.ም፡ ነበር።የመጀመርያው፡የኦሎምፒክ፡ተሳትፎአችን፡የአውስትራሊያው፡ሜልቦርን፡ኦሎምፒክ፡ሲሆን፡ኢትዮጵያ፡በማራቶን፡ውድድር፡አትሌት፡ባሻዬ፡ፈለቀ፡እና፡ብርሃኑን፡አሰለፈች።
እስከ፡አሁንም፡ዓለምን፡እያስደነቀ፡ያለው፡የኢትዮጵያ፡አትሌቶች፡አይበገሬነት፡በሜልቦርን፡ተጀምሮ፡በ1960ዓ.ም፡በሮም፡ኦሎምፒክ፡በአበበ፡ቢቂላ፡ድል፡አድራጊነት፡የመጀመርያው፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ለኢትዮጵያ፡ለአፍሪካ፡በማስገኘት፡ዛሬም፡ላለው፡ድላችን፡በር፡ከፋች፡ሆነ።
በባዶ፡እግሩ፡ማራቶንን፡የሚያክል፡ከባድ፡ውድድር፡በሚያስደንቅ፡ፍጥነት፡የሞሮኮውን፡አትሌት፡ከሗላው፡አስከትሎ፡በመገባት፡የኦሎምፒክ፡ባለ፡ድል፡ከመሆኑም፡ሌላ፡አዲስ፡የዓለም፡የማራቶን፡ክብረወሰን፡ባለቤት፡ሆነ።
የአበበ፡ስም፡እየገነነ፡እና፡በየተሰለፈበት፡ውድድር፡ሁሉ፡ድልን፡እየተቀዳጀ፡መጣ፡ አይደርስ፡የለምና፡ አራት፡ዓመት፡ቆይቶ፡በ1964ዓ.ም፡ የጃፓኑ፡ቶክዮ፡ኦሎምፒክ፡ደረሰ፡አሁንም፡ሞት፡እንጂ፡ሰው፡ያላሸነፈው፡አበበ፡ቢቂላ፡የሁሉንም፡ሃገር፡አትሌቶች፡ቀድሞ፡በመግባት፡ለእናት፡ሃገሩ፡ሁለተኛውን፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ከአዲስ፡የማራቶን፡ክብረወሰን፡ጋር፡አስገኘ።
አበበ፡ሁለተኛውን፡ኦሎምፒክ፡ስያሸንፍ፡የትርፍ፡አንጀት፡ቀዶ፡ጥገና፡አድርጎ፡ከሆስፒታል፡ከወጣ፡በጥቂት፡ሳምንታት፡ውስጥ፡መሆኑ፡ሌላው፡አስደናቂ፡ታሪክ፡ሆነ።
ከሮም፡ኦሎምፒክ፡ወቅት፡ጀምሮ፡በስዊዲናዊው፡ማጆር፡ኦኒስ፡ኒስካንን፡ አሰልጣኝ፡ይለማመዱ፡የነበሩት፡አበበ፡ቢቂላ፤ማሞ፡ወልዴ፤ዋሚ፡ብራቱ፤ደምሴ፡ወልዴ፤ሰብስቤ፡ማሞ፤ተገኝ፡በዛብህ፡አሁንም፡ልምምዳቸውን፡በመቀጠል፡በ1968ዓ.ም፡ወደ፡ሜክሲኮ፡ኦሎምፒክ፡በረሩ።
በሜክሲኮ፡ኦሎምፒከክ፡ለኢትዮጵያ፤ሌላ፡አዲስ፡ድል፡ተመዘገበ፡ማሞ፡ወልዴ፡በ10.000 ሜትር፡የብር፡ሜዳልያ፡አስገኘ፡በማራቶን፡ውድድር፡አበበ፡እና፡ማሞ፡አብረው፡ተሰለፉ፡በውድድሩ፡አጋማሽ፡ገደማ፡ጀግናው፡አበበ፡ህመም፡ስለተሰማው፡ወደ፡ማሞ፡ጠጋ፡ብሎ፡ማሞ፡ይህን፡ውድድር፡አሸንፈህ፡የሃገራችን፡ባንዲራ፡መውለብለቡን፡እምዲቀጥል፡አድርግ፡ብሎት፡ከውድድሩ፡ወጣ ፤ማሞም፡አደራውን፡ተቀብሎ፡አበበን፡በመተካት፡በቀዳሚነት፡ኦሎምፒክ፡ስታዲየም፡ደረሰ፡ሶስታኛው፡የማራቶን፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ለኢትዮጵያ፡ሆነ።
ማራቶን፡እና፡ኢትዮጵያ፡ኢትዮጵያ፡እና፡ማራቶን፡የማይነጣጠሉ፡የአንድ፡ሳንቲም፡ሁለት፡ገጽታዎች፡ሆኑ።ሶስት፡የኦሎምፒክ፡ማራቶን፡በተከታታይ፡ያአሸኘፈች፡ብቸኛ፡ሃገር፡እስከ፡አሁንም፡፡ኢትዮጵያ፡ብቻ፡ናት።

No comments: