መስከረም፡21ቀን፡የዛሬ፡ሳምንት፡በቤልጂየም፡ዋና፡ከተማ፡በብራስልስ፡ለሚካሄደው፡ዓመታዊ፡የዓለም፡ግማሸ፡ማራቶን፡ውድድር፡አትሌቶቻችን፡በከፍተኛ፡ዝግጅት፡ላይ፡መሆናቸው፡ተገለጠ።
ውድድሩ፡የሚካሄደው፡በሁለቱም፡ጾታ፡ሲሆን፡በወንዶች፡የአዋቂና፡የወጣት፡ተወዳዳሪዎች፡ተካፋይ፡ይሆናሉ፡፡
በዚህ፡ውድድር፡በሴቶች፡ሶስት፡-በአዋቂ፡ወንዶች፡አምስት፡በወጣት፡ወንዶች፡አራት፡በድምሩ፡12አትሌቶች፡ዝግጅታቸውን፡እያጧጧፉ፡ናቸው፡፡
በአዋቂ፡ወንዶች፡ለዚህ፡ውድድር፡የተመረጡት፡ኪዳኔ፡ገ/ሚካኤል፡ አዱኛ፡አጥናፉ፡ ወልደስላሴ፡ሚልኬሳ፡ ፍራንሷ፡ወልደማርያምና፡ ይኩን፡ገ/መስቀል፡ናቸው፡፡
በወጣት፡ወንዶች፡የተመረጡት፡ ብሩክ፡በቀለ፡ ተገኑ፡አበበ፡ ፍቃዱ፡ይፍሩና፡፡ልኡልስግድ፡ወልደማሪያም፡ሲሆኑ፡በሴቶች፡
የሚካፈሉት፡ፋንታዬ፡ሲራክ፡፡ አይሻ፡ጊጊና፡ አሰለፈች፡አሰፋ፡መሆናቸው፡ታውቋል፡፡
የዓለም፡ግማሽ፡ማራቶን፡ውድድር፡በተለያዩ፡ሃገሮች፡በያመቱ፡የሚካሄድ፡ሲሆን፡አትሌቶቻችን፡በተካፈሉብት፡ቦታ፡ሁሉአጥጋቢ፡ውጤት፡እያስመዘገቡ፡መመለሳቸው፡ይታወሳል፡፡ በዚህ፡ውድድርም፡ተመሳሳይ፡ድል፡እንዲያስመዘግቡ፡ዝግጅት፡ክፍላችን፡
መልካም፡ምኞቱን፡ይገልጣል፡፡
አዲስ፡ዘመን፡ መስከረም፡ 14 ቀን 1986 ዓመተ፡ምህረት፡
the green flood
Friday, August 29, 2008
Monday, August 25, 2008
Wednesday, August 6, 2008
Wednesday, July 16, 2008
Monday, July 14, 2008
Wednesday, June 4, 2008
አለሚቱ፡በቀለ፡አጋ፡በብራስልስ፡20ኪ.ሜ የሩጫ፡ውድድር፡፡2ኛ፡ወጣች።
አለሚቱ፡የደረሰባትን፡የጡንቻ፡ህመም፡በመቋቋም፡የቡሩጅ፡አስር፡ማይል፡ውድድርንም፡ባለፉት፡ስድስት፡አመታተ፡በራሷም፡ሆነ፡በሌሎች፡አትሌቶች፡ከተመዘገበው፡ሰአት፡የተሻለ፡በመሮጥ፡የዚህ፡አመት፡አሸናፊ፡ለመሆን፡ችላለች።
Sunday, May 18, 2008
የአበበ፡ቢቂላ፡አትሌቲከሰ፡ክለብ፡በአንትወርፕን፡አሸነፈ፡
አፕሪል፡20/2008 በቤልጂየም፡አገር፡ሁለተኛው፡ከተማ፡በሆነችው፡በአንትወርፕን፡በተዘጋጀው፡የማራቶን፡ዱላቅብብል፡በዚያው፡ከተማ፡የተቋቋመው፡የአበበ፡ቢቂላ፡ክለብ፡በወንዶች፡ቀድሞ፡በመግባት፡ድልን፡ተቀዳጅቷል።ክለቡን፡በመወከል፡የተወዳደሩት፡አትሌቶች፡ከቤልጂምና፡ከኔዘርላንድ፡ተውጣጡ፡ናቸው።
ሀይሌን፡እንቅደመው፡
የፊታችን፡ሳምንት፡በጃፓን፡አገር፡በሚዘጋጀው፡የህይሌን፡እንቅደመው፡የማራቶን፡ዱላ፡ቅብብል፡ጃፓናዊያን፡በመሳተፍ፡የሚያሰባስቡት፡ብር፡ለአፍሪካ፡መርጃ፡እንደሚውል፡ተረጋግጦዋል፡አትሌት፡ ሀይሌ፡ገብረስላሴ፡በዚያን፡ወቅት፡ለኦሎምፒክ፡ሰአት፡ለማምጣት፡በሆላንድ፡አገር፡ሄንጌሎ፡10000ሜትር፡ስለሚወዳደር፡በእለቱ፡የራሱን፡ማራቶን፡ውድድር፡በቪድዬ፡መልክ፡እንደሚልክላቸው፡ተናግሮአል፡ተወዳዳሪዎች፡በዳኛ፡ሚወሰንላቸውን፡ርቀት፡ለሶስት፡በመሮጥ፡የሀይሌን፡ክብረወሰን፡ለመስበር፡ይሞክራሉ፡ተብሎ፡ይጠበቃል።
Monday, May 12, 2008
Thursday, May 1, 2008
Tuesday, April 29, 2008
Tuesday, April 22, 2008
Monday, April 14, 2008
Friday, April 11, 2008
Monday, April 7, 2008
Saturday, April 5, 2008
Friday, April 4, 2008
የቤተሰብ፡ውርስ፡እየሆነ፡የመጣው፡የሃገራችን፡አትሌቲክስ፡ስፖርት፡
ከአለፉት፡ጥቂት፡ዓመታት፡ወዲህ፡በተደጋጋሚ፡የምንሰማው፡የሃገራችን፡አትሌቶች፡ሩጫን፡የቤተሰብ፡ስራ፡የማድረግ፡ሁኔታ፡ከግዜ፡ወደ፡ግዜ፡እየጨመረ፡መጥቶአል።
ደራርቱ፡ቱሉ፡ከባርሴሎና፡መልስ፡በሰጠችው፡ቃለ፡መጠይቅ፡ከእኔ፡የበለጠ፡የምትሮጥ፡እህቴ፡አለች፡ብላ፡ነበር፡ሙሉ፡ቱሉ፡ግን፡አልገፋችበትም።
በተደጋጋሚ፡የዓለም፡ወጣቶች፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡ሻምፒዬን፡የነበረው፡የፍስሃ፡አበበ፡ወንድም፡ታደለ፡አበበ፡በተለይ፡በሃገር፡ውስጥ፡ችሎታውን፡አስመስክሮ፡ነበር።
ከ1500ሜትር፡እስከ፡ማራቶን፡ድረስ፡በዓለም፡ደረጃ፡ታዋቂ፡የነበረው፡የወዳጆ፡ቡልቲ፡ወንድሞች፡ገለቱ፡ቡልቲ፡እና፡ኩምሳ፡ቡልቲ፡እምብዛም፡አልተሳካላቸውም።
የጀግናው፡የበቀለ፡ደበሌ፡ወንድሞች፡ዘውዴ፡እና፡አሰፋ፡ደበሌ፡ወደ፡ኢንተርናሸናል፡መድረክ፡ሳይወጡ፡ቀሩ።
የታላቁ፡አትሌት፡የህይሌ፡ገብረስላሴ፡ወንድም፡ተክዬ፡ገብረስላሴ፡እና፡እህቱ፡የሺ፡ገብረስላሴ፡በዓለም፡ሻምፒዮናዎች፡የማይናቅ፡ውጤት፡አስመዝግበዋል፡በላይ፡ገብረስላሴ፡ግን፡አልተሳካለትም።
በአሜሪካ፡ሃገር፡ታላቅ፡ስም፡ነበረው፡፡የሃይሉ፡ኤባ፡ወንድም፡ጥላሁን፡ኤባ፡ሃገራችንን፡እስከ፡መወከል፡ደርሶ፡ነበር፡ግሩም፡ኤባ፡ግን፡ብዙ፡አልገፋበትም።
ጠንካራዎቹ፡ሃብቴ፡ጂፋር፡እና፡ተስፋዬ፡ጂፋር፡የሃገራችንን፡ስም፡በብዙ፡ቦታዎች፡በተደገጋጋሚ፡አስጠርተዋል፡አሁንም፡በማስጠራት፡ላይ፡ናቸው።
አሰፋ፡መዝገቡ፡እና፡አየለ፡መዝገቡ፡በጉብዝናቸው፡ከሃገር፡አልፎ፡በዓለም፡አቀፍ፡ደረጃ፡ተመሰከረላቸው፡ጠንካራ፡አትሌቶች፡እንደነበሩ፡የቅርብ፡ግዜ፡ትዝታ፡ነው።መኮንን፡ቱሉ፡እና፡ብርሃኑ፡ቱሉም፡እንዲሁ። world and olimpic marathon champion gezahgen abera and his yungest brother daneil abera who run under 2h10 . እንዲህ፡እያለ፡ሲቆጠር፡ብዙ፡ልንል፡እንችላለን፡የቀነኒሳ፡በቀለ፡እና፡ታሪኩ፡በቀለ፡ጉዳይ፡ገና፡እያስደነቀ፡ያለ፡የዘመናችን፡የአትሌቲክስ፡ዜና፡ነው፡ገና፡ብዙ፡እናያለን።
በታላቅ፡እህት፡በበቀሉ፡ዲባባ፡የተጀመረው፡የእጅጋየሁ፡ዲባባ፡እና፡የጥሩነሸ፡ዲባባ፡ገና፡ተነግሮ፡ሳያበቃ፡ትንሿ፡ገንዘቤ፡ዲባባ፡የወጣቶች፡አሸናፊ፡በመሆን፡የወርቅ፡ሜዳሊያ፡አስገኝታለች።ገና፡ከአንድ፡ቤተሰብ፡ሁለት፡ሲገርመን፡ዛሬ፡ጭራሸ፡አራት፡ሆነዋል ፣ ሲሳይ በዛብህ ፣ አለማየሁ በዛብሀ ፣አለምገና በዛብሀ፣ መስታወት ቱፋ ፣ ትእግስት ቱፋ ፣ ይህ፣የሚያመለክተን፡ሃገራችን፡ሁኔታዎቸን፡ብታመቻች፡ብዙ፡ድንቅ፡አትሌቶችን፡ማፍራት፡እንደምንችል፡ነው።በቤተሰብ፡እየታየ፡ያለው፡ሁኔታ፡ደግሞ፡ማንም፡አዲስ፡አትሌት፡በቀደምቶች፡ወይም፡በታላላቆቻቸው፡ከተደገፉ፡ያለምንም፡መሰናክል፡ብቃት፡ያላቸው፡አትሌቶች፡እንደሚወጣቸው፡ነው።

Thursday, April 3, 2008
ኢትዮጵያዊያን የማያውቃቸው ታላላቅ አትሌቶቻችን
ሃገራችን፡ታላቋ፡የሩጫ፡ሃገር፡የሚለውን፡ስም፡ለማግኘት፡የቻለችበት፡ምክንያት፡ለማንም፡ሰው፡ግልጽ፡ነው።ኢትዮጵያ፡ሃገራችን፡በተለያዩ፡ኢንተርናሽናል፡ውድድሮች፡መሳተፍ፡ከጀመረች፡ከግማሽ፡ምእተ፡ዓመት፡በላይ፡አስቆጥራለች።የኢትዮጵያ፡አትሌቶች፡ድልንም፡መጎናጸፍ፡የጀመሩት፡ከመጀመሪያ፡ተሳትፎ፡ማግስት፡ሲሆን፡ይህ፡ከሃምሳ፡ዓመታት፡በላይ፡የቆየውና፡ሲወራረስ፡የመጣው፡ጀግንነት፡ዛሬም፡ይበልጡኑ፡እየጎለበተና፡እየተጠናከረ፡መጥቶ፡በየተሰለፉበት፡ውድድር፡መድረክ፡ሁሉ፡አልበገሬነታቸው፡ዓለምን፡የሚያስደንቅ፡እየሆነ፡መጥቷል።
ዛሬ፡የኢትዮጵያ፡እና፡የኬንያ፡አትሌቶች፡የማይሳተፉበት፡ውድድር፡ሁሉ፡አይደምቅም፡በስነምግባር፡የታነጹት፡የሃገራችን፡ልጆች፡አረንጓዴ፡ቢጫ፡ቀዩ፡ባንዲራችንን፡ከፍ፡በማድረግ፡በድህነት፡በጦርነት፡በረሃብ፡የምትታወቀውን፡የኢትዮጵያ፡ሰንደቅ፡ዓላማዋ፡ከሃያላን፡ሃገሮች፡በላይ፡እንዲውለበለብ፡እያደረጉ፡ናቸው።ይህ፡ጀግንነት፡ከምን፡የመጣ፡ነው፡?አመጋገባቸው፡ምንድን፡ነው፡?የልምምዳቸው፡ሁኔታ፡እንዴት፡ነው፡?የሚሉት፡ጥያቄዎች፡በብዙ፡የስፖርት፡ተመራማሪዎች፡እና፡ባለሙዎች፡ዘንድ፡መነሳት፡ከጀመረ፡ሰንብቷል።ግን፡ከመንፈሰ፡ጠንካራነታችንና፡ከጽኑ፡የሃገር፡ፍቅራችን፡በቀር፡ምንም፡ድብቅ፡ሚስጢር፡እንደሌለ፡በእርግጠኝነት፡ለመናገር፡እወዳለሁ።ብዙ፡የሃገራችን፡ህዝብ፡የማያውቃቸው፡በዓለም፡ታላላቅ፡ውድድሮች፡ላይ፡በመሰለፍ፡ከፍተኛ፡ድል፡ያስመዘገቡ፡በርካታ፡አትሌቶች፡አሉን፡ዛሬ፡ግን፡የት፡ናቸው፡? አረንጓዴው፡ጎርፍ"፡"THE GREEN FLOOD" የደጋ፡በራሪዎቸች፡ የሰማይ፡ዳርቻ፡የማይበግራቸው፡እና፡የመሳሰሉትን፡ስም፡ ያገኘንበትን፡ከ1970ዎች፡አጋማሽ፡ጀምሮ፡እስከ፡1980ዎቹ፡አጋማሸ፡ድረስ፡ያሉትን፡ዓመታት፡ብቻ፡እንኻን፡ብንመለከት፡ሃገራችን፡የብዙ፡ጀግኖች፡ሃገር፡መሆኗን፡ቢያንስ፡እንገነዘባለን።ከዚያ፡ዛሬ፡የትና፡በምን፡ሁኔታ፡ይገኛሉ፡የሚሉትን፡ጥያቄዎችን፡ለመመለስ፡ይቀለናል።
የሃገራችን፡አትሌቶች፡አረንጓዴ፡ለብሰው፡ተከታትለው፡በመግባት፡ከአንድ፡እስከ፡ዘጠኝ፡በአዋቂ፡፡ከአንድ፡እስከ፡ስድስት፡በወጣቶች፡የአለውን፡ቦታ፡አላስቀምስ፡ያሉበት፡ወቅት፡ነበር፡The Greenflood የሚለውን፡ስም፡ያሰጣቸው።እነ፡ግርማ፡ወልደሃና፡ ሀይሉ፡ወልደጻዲቅ፡ ወልዴ፡ሮበሌ፡ ቶሎሳ፡ቆቱ፡ ተክሌ፡ፈንቴሳ፡ አብርሃም፡ታደሰ(ፉል) እሸቱ፡ቱራ፡ መሃመድ፡ከዲር፡ምሩጽ፡ይፍጠር፡ ብርሃኑ፡ግርማ፡ ከበደ፡ባልቻ፡ ደጀኔ፡በየነ(ሾላ)፡ ደረጀ፡ነዲ፡ ስዩም፡ንጋቱ፡ ካሳ፡ባልቻ፡ ወዳጆ፡ቡልቲ፡ በቀለ፡ደበሌ፡ ጫላ፡ኡርጌሳ፡ አዱኛ፡ለማ፡ ፍስሃ፡አበበ፡ ነጋሽ፡ሃብቴ፡ ዙርባቸው፡ገላው፡ አራርሳ፡ፉፋ፡ አንጋሶ፡ታልጋ፡እና፡ሌሎችም፡ይገኙበታል።
ከእነዚህ፡አትሌቶች፡ውስጥ፤አብዛኛዎቹ፡በኢንተርናሸናል፡ደረጃ፡ከፍተኛ፡እውቅና፡የነበራቸውና፡በመደጋገም፡ የዓለም፡እና፡ የዓህጉር፡ ሻምፒዮና፡ሜዳሊያዎችን፡የተሸለሙ፡ሲሆኑ፡በዚያ፡ወቅት፡ሃገራችን፡ትከተል፡በነበረው፡የሶሻሊዝም፡ስርዓት፡የተነሳ፡በ10000ሜትር፡በ5000ሜትር፡በ3000መሰናክል፡በማራቶን፡እንዲሁም፡በእርምጃ፡ውድድር፡ የኦሎምፒክ፡ሜዳሊያ፡ማስገኘት፡እየቻሉ፡በፖሎቲካ፡ምክንያት ፡የሎስአንጀለስንና፡የሴኡልን፡ኦሎምፒኮች፡ሳይሳተፉ፡ቀርተዋል።
በዚያን፡ወቅት፡ኢትዮጵያ፡በሶምሶማ፡ወይም፡በእርምጃ፡ውድድር፡በተለይ፡በአፍሪካ፡ሻምፒዬናዎች፡ለብዙ፡ዓመታት፡በተከታታይ፡ያሸንፉ፡የነበሩ፡በአውሮፓና፡በሌሎች፡አህጉራት፡ብዙ፡ድል፡የተቀዳጁት፡ ሁንዴ፡ጦሬ፡ ሸምሱ፡ሃሰን፡እንዲሁም፡ተተኪዎቹ፡በቀለ፡ሁንዴ፡እና፡ በድሩ፡ከፍተኛ፡ችሎታ፡የነበራቸው፡አትሌቶች፡ነበሩ።
ይህ፡እግዲህ፡ በደርግ፡ዘመነ፡አገዛዝ፡ነበረውን፡ሁኔታ፡የሚዳስስ፡ሲሆን፡ከዚያ፡በፊት፡የነበሩትን፡የኦሎምፒክ፡ተሳትፎ፡በሚለው፡ጽሁፍ፡ስማቸውን፡በመጠኑ፡ለመጥቀስ፡ሞክሬአለሁ፡በእነ፡አበበና፡በአረንጓዴ፡ጎርፍ፡መሃል፡ደግሞ፡ራሱን፡የቻለ፡የእነ፡ባሻ፡ፍቅሩ፡ደገፋ፡ ባሻ፤ውሂብ፡ማስረሻ፡ ሸብሩ፡ረጋሳ፡ሮበሌ፡ጉርሙ፡እና፡መሳሰሉት፡የሮጡበት፡ዘመን፡ነበር።
ከአበበ፡ቢቂላ፡በስተቀር፡ዋሚ፡ቢራቱና፡ባሻ፡ፈለቀን፡ማሞን፡ጨምሮ፡በአካል፡አግኝቼ፡የመነጋገር፡እድሉ፡ስላገኘሁ፡ደስ፡ይለኛል፡ድርሻቸውን፡ታሪክ፡ሰርተው፡ካለፉት፡ሌላ፡በህይወት፡ያሉት፡በምን፡ሁኔታ፡እንዳሉ፡ሳስብ፡በጣም፡አዝናለሁ።የኔ፡ማዘን፡ግን፡ኑሮአቸውን፡አይቀይርም። አዲሶቹ፡እና፡እኛ፡ብንተባበር፡ግን፡አሮጌዎቹ፡ይታደሳሉ፡የሚል፡እምነት አለኝ ::
Wednesday, April 2, 2008
Sunday, March 30, 2008
Friday, March 28, 2008
Wednesday, March 26, 2008
36ኛው፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ሩጫ፡፡በኤዲንበርግ፡ይደረጋል።
እ.ኤ.አ.ማርች፡30/2008ዓ.ም፡ በሚጀመረው፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡ከሚሰለፉት፡ሃገሮች፡ውስጥ፡ጠንካራው፡ የኢትዮጵያ፡ቡድን፡መሆኑን፡ብዙዎች፡ይገምታሉ፡በዚህ፡በ36ኛው፡ኤዲንበርጉ፡የዓለም፡ሃገር፡አቋራጭ፡ውድድር፡የኬንያ፡ቡድን፡ቢሳተፍም፡በሃገሪቱ፡በተፈጠረው፡የፖለቲካ፡ውዝግብ፡የተነሳ፡በስነልቦና፡ዝግጅት፡ከቀድሞው፡ባነሰ፡ጥንካሬ፡እንደሚቀርብ፡ይገመታል፡በቅርቡ፡በተደረገው፡የቤት፡ውስጥ፡የዓለም፡ሻምፒዮና፡ይህው፡ታይቶ፡ነበር።
የኤርትራ፡ቡድን፡በጠንካራው፡አትሌት፡ዘረሰናይ፡ታደሰ፡ዘንድሮም፡የአምናውን፡ድል፡ላለማስነጠቅ፡እንደሚተጋ፡ይጠበቃል።በመቀጠል፡የሞሮኮ፡ቡድን፡በሰልጣኝ፡ኢብራሂም፡ቡላሚ፡አማካኝነት፡በአዲስ፡መልክ፡የተመረጡ፡በአብዛኛ፡ወጣት፡የሆኑ፡አትሌቶችን፡ይዞ፡ይሰለፋል።
በዚህ፡ዓመት፡ከኤርትራው፡ዘረሰናይ፡በስተቀር፡ለኢትዮጵያ፡ቡድን፡ሌላ፡የሚያሰጋ፡እንዳሌለ፡ብዙዎች ፡ይተነብያሉ።በቀነኒሳና፡በጥሩነሽ፡የሚመራው፡የኢትዮጵያ፡ቡድን፡ በድል፡እንደሚመለስ፡ይጠበቃል።

Monday, March 24, 2008
የኢትዮጵያ፡አትሌቶች፡የኦሎምፒክ፡ተሳትፎ፡
ኢትዮጵያ፡አትሌቶችን፡ለኦሎምፒክ፡ውድድር፡መላክ፡የጀመርችው፡እንደ፡አውሮፓዊያን፡አቆጣጠር፤በ1956 ዓ.ም፡ ነበር።የመጀመርያው፡የኦሎምፒክ፡ተሳትፎአችን፡የአውስትራሊያው፡ሜልቦርን፡ኦሎምፒክ፡ሲሆን፡ኢትዮጵያ፡በማራቶን፡ውድድር፡አትሌት፡ባሻዬ፡ፈለቀ፡እና፡ብርሃኑን፡አሰለፈች።
እስከ፡አሁንም፡ዓለምን፡እያስደነቀ፡ያለው፡የኢትዮጵያ፡አትሌቶች፡አይበገሬነት፡በሜልቦርን፡ተጀምሮ፡በ1960ዓ.ም፡በሮም፡ኦሎምፒክ፡በአበበ፡ቢቂላ፡ድል፡አድራጊነት፡የመጀመርያው፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ለኢትዮጵያ፡ለአፍሪካ፡በማስገኘት፡ዛሬም፡ላለው፡ድላችን፡በር፡ከፋች፡ሆነ።
በባዶ፡እግሩ፡ማራቶንን፡የሚያክል፡ከባድ፡ውድድር፡በሚያስደንቅ፡ፍጥነት፡የሞሮኮውን፡አትሌት፡ከሗላው፡አስከትሎ፡በመገባት፡የኦሎምፒክ፡ባለ፡ድል፡ከመሆኑም፡ሌላ፡አዲስ፡የዓለም፡የማራቶን፡ክብረወሰን፡ባለቤት፡ሆነ።
የአበበ፡ስም፡እየገነነ፡እና፡በየተሰለፈበት፡ውድድር፡ሁሉ፡ድልን፡እየተቀዳጀ፡መጣ፡ አይደርስ፡የለምና፡ አራት፡ዓመት፡ቆይቶ፡በ1964ዓ.ም፡ የጃፓኑ፡ቶክዮ፡ኦሎምፒክ፡ደረሰ፡አሁንም፡ሞት፡እንጂ፡ሰው፡ያላሸነፈው፡አበበ፡ቢቂላ፡የሁሉንም፡ሃገር፡አትሌቶች፡ቀድሞ፡በመግባት፡ለእናት፡ሃገሩ፡ሁለተኛውን፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ከአዲስ፡የማራቶን፡ክብረወሰን፡ጋር፡አስገኘ።
አበበ፡ሁለተኛውን፡ኦሎምፒክ፡ስያሸንፍ፡የትርፍ፡አንጀት፡ቀዶ፡ጥገና፡አድርጎ፡ከሆስፒታል፡ከወጣ፡በጥቂት፡ሳምንታት፡ውስጥ፡መሆኑ፡ሌላው፡አስደናቂ፡ታሪክ፡ሆነ።
ከሮም፡ኦሎምፒክ፡ወቅት፡ጀምሮ፡በስዊዲናዊው፡ማጆር፡ኦኒስ፡ኒስካንን፡ አሰልጣኝ፡ይለማመዱ፡የነበሩት፡አበበ፡ቢቂላ፤ማሞ፡ወልዴ፤ዋሚ፡ብራቱ፤ደምሴ፡ወልዴ፤ሰብስቤ፡ማሞ፤ተገኝ፡በዛብህ፡አሁንም፡ልምምዳቸውን፡በመቀጠል፡በ1968ዓ.ም፡ወደ፡ሜክሲኮ፡ኦሎምፒክ፡በረሩ።
በሜክሲኮ፡ኦሎምፒከክ፡ለኢትዮጵያ፤ሌላ፡አዲስ፡ድል፡ተመዘገበ፡ማሞ፡ወልዴ፡በ10.000 ሜትር፡የብር፡ሜዳልያ፡አስገኘ፡በማራቶን፡ውድድር፡አበበ፡እና፡ማሞ፡አብረው፡ተሰለፉ፡በውድድሩ፡አጋማሽ፡ገደማ፡ጀግናው፡አበበ፡ህመም፡ስለተሰማው፡ወደ፡ማሞ፡ጠጋ፡ብሎ፡ማሞ፡ይህን፡ውድድር፡አሸንፈህ፡የሃገራችን፡ባንዲራ፡መውለብለቡን፡እምዲቀጥል፡አድርግ፡ብሎት፡ከውድድሩ፡ወጣ ፤ማሞም፡አደራውን፡ተቀብሎ፡አበበን፡በመተካት፡በቀዳሚነት፡ኦሎምፒክ፡ስታዲየም፡ደረሰ፡ሶስታኛው፡የማራቶን፡የወርቅ፡ሜዳልያ፡ለኢትዮጵያ፡ሆነ።
ማራቶን፡እና፡ኢትዮጵያ፡ኢትዮጵያ፡እና፡ማራቶን፡የማይነጣጠሉ፡የአንድ፡ሳንቲም፡ሁለት፡ገጽታዎች፡ሆኑ።ሶስት፡የኦሎምፒክ፡ማራቶን፡በተከታታይ፡ያአሸኘፈች፡ብቸኛ፡ሃገር፡እስከ፡አሁንም፡፡ኢትዮጵያ፡ብቻ፡ናት።

Sunday, March 23, 2008
የኢትዮጵያ፡አትሌቲክስና፡አትሌቶች፡ከየት፡ወዴት።
የአገራችን አትሌቶች የማይካፈሉበት ውድድር አይደምቅም እነሱ በደርሱበት ቦታ ሁሉ ባንዲራችን ክፍ ብላ ትውለበለባለች ይህቺ ሃገር በየዘመኑ ዓለምን የሚያስደንቅ ችሎታ ያላቸው አትሌቶች አጥታ አታውቅም፣፣
የሃገራችን አትሌቲክስ ስፖርት የተጀመረው በጦር ስራዊቱ አካባቢ እንደሆነ የሚጠቁሙ ብዙ ማረጋገጫዎች እናገኛልን
ከ1956 አውስትራሊያው ኦሊምፒክ ጫወታዎች ማግስት ጀምሮ ማራቶን የሚል ቃል በብዛት ይስማ ጀመር፣፣ ሁለተኛው የሃገራችን የ1960 የሮማ ኦሊምፒክ ግን ተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም የመጀመሪያው ኦሊምፒክ ድል ሆነ ከዚያም መቀጠል በ1964 ቶኪዮ በራሱ ጀግናው በአበበ ቢቂላ ተደገመ የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ ማራቶን የማራቶን ጉዳይ ሲነሳ ኢትዮጵያ የማይነጣጠሉ ሆኑ ከአራት ዓመት ቦሃላም ማሞ ሶስተኛውን የኦሊምፒክ ወርቅ ለሃገራችን አመጣ ማሞ በዚያ ብቻ አላበቃም በዘመኑ ነሃስም አስገኝቶልናል ፣፣
በእነ በሻይ ፈለቀ ገብረ የተጀመረው እነ አበበን ፣ ማሞን ፣ ደምስን ፣ሽበሺን፣ ተገኝ በዛብህን አስከትሎ ለነምሩጽ ይፍጠር ዘመን ስንደርስ ከማራቶን ወደ አስር አና አምስት ሺህ ሜትር በመሸጋገር ኢትዮጵ ያዊያን አትሌቶች በየተሰለፉበት የውድድ ር መ ድረክ ሁሉ ድልን መቀዳጀት የተለመደ ሆነ ::

Subscribe to:
Posts (Atom)